የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት “ንግድ ለሰላም ግንባታ ያለው ፋይዳ” በሚል ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርጓል።
በመርሃ ግብሩም የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ዘሀራ መሀመድ፤ ምክር ቤቱ መንግስትና የንግዱ ማህበረሰብ ተቀራርበው እንዲሰሩ ድልድይ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፣ “ንግድ ለሰላም” በሚል የተደረገው ምክክርም የንግዱ ማህበረሰብ በሀገር ሰላም ላይ የራሱን አስተዋፅኦ እንዲያበረክት የሚያግዝ ነው ብለዋል።

ሰላም ለችግሮቻችን መፍቻ ቁልፍ ስለመሆኑ ያነሱት የኢትዮጵያ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሀፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ፤ የንግዱ ዘርፍ የስራ እድልን በመፍጠር፣ የስራ አጥን ቁጥር በመቀነስ በኩል ድርሻው የላቀ ነውም ብለዋል።
በዚህም በሀገር ሰላም ላይም በጎ አበርክቶውን ማሳረፍ ይገባዋል ሲሉም አንስተዋል።
በሀገር ሰላም ላይ ሁሉም የበኩሉን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባውም ተመላክቷል።
በፅዮን ማሞ