ኢትዮጵያ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ ኢ-ፍትሐዊ እና ታሪካዊ ስህተት ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ ኢ-ፍትሐዊ እና ታሪካዊ ስህተት ነው
  • Post category:ፖለቲካ

AMN – ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያ የባህር በሯን ያጣችበት መንገድ ኢ-ፍትሐዊና ታሪካዊ ስህተት መሆኑን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ ገለጹ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ የባህር በር ማጣት ከሸቀጥ ጋር ብቻ የተያያዘ አለመሆኑንና ይልቁንም የፖሊሲ ነጻነቷን የሚጋፋ፣ ኢኮኖሚያዊ ጫና የሚፈጥር የሉዓላዊነት ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም መንግስት ኢትዮጵያ መልሳ የባህር በር ባለቤት እንድትሆን በሰላማዊና በሰጥቶ መቀበል መርህ የተመሰረተ አቋም መያዙን ተናግረዋል፡፡

በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ መሰረት ኃይሌ፤ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የባህር በር ባለቤትነቷን ለማረጋገጥ እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ዓላማን በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ማሳካት ግዴታችን ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ምክትል አፈ ጉባኤ ሎሚ በዶ፤ መንግስት በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የሚያደርገውን ጥረት የኢትዮጵያ ህዝብ ሊደግፍ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ በፓርላማ ዲፕሎማሲ፣ ደጋፊ አዋጆችን በማውጣትና ፖሊሲዎችን በመገምገም ለመንግስት ጥረት ተግባራዊነት ሚናውን ይወጣል ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review