ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው !

You are currently viewing ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ሀገራዊ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው !

AMN- ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም

መንግሥት ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማምረት እንዲቻል የተኪ ምርት ስትራቴጂን በመቅረጽ ወደ ሥራ በመግባቱ ከፍተኛ ውጤቶች ተመዝገበዋል ።

ስትራቴጂው የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲኖር፣ የወጪ-ገቢ ምርት እንዲመጣጠን እና ሀገራዊ ሉዓላዊነት እንዲረጋገጥ እያደረገ ይገኛል።

በተለይ በውስጥ አቅም መቅረብ የሚችሉ ዋና ዋና የገቢ ምርቶች ተለይተው ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ ምርቶች እንዲተኩ ተኩረት መደረጉ የውጪ ምንዛሬ ከማዳን እና ከሥራ እድል ፈጠራ አንጻር ፋብሪካዎችን ተወዳዳሪና ውጤታማ እንዲሆኑ አድርጓል ።

የተኪ ምርት ስትራቴጂ በሁሉም ዘርፍ በተሟላ መልኩ ገቢራዊ መደረጉ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፉ የተሻለ የሥራ ዕድል አጋጣሚ የተፈጠረ ሲሆን ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በተለያዩ ዘርፎች በተኪ ምርት ላይ በተከናወኑ ሥራዎች 1 ነጥብ 08 ቢሊየን የአሜርካን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ማዳን መቻሉን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

በሀገራችን ነባራዊ የፍጆታ ፍላጎት አንፃር የትኞቹ ምርቶች በቅድሚያ ይተኩ በሚል በምግብ እና መጠጥ፣ በጨርቃጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ፣ በኪሚካልና ኮንስትራክሽን ፣ ብረታብረት ብረት እና ቴክኖሎጂ ላይ በማተኮር 96 ተወዳዳሪ ተኪ ምርቶች ተለይተው በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የተደረገው ጥረት እንደሀገር ፍሬ እያፈራ ይገኛል ።

ለአብነት የጥጥ ምርትን ፍላጎት ሙሉበሙሉ በሀገር ውስጥ ምርት ለመሸፈን በአፋር ክልል አሚበራና ወረር ወረዳዎች በ2017/18 የምርት ዘመን በ110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥሬ ጥጥ 1.9 ሚሊዮን ኩንታል የተገኘ ሲሆን ዘንድሮው የምርት ዘመን ለኢንደስትሪዎች የሚፈለገውን ያህል የጥጥ ምርት በመጠንና በጥራት ማቅረብ ተችሏል ፡፡

የማኑፋክቸሪግ ኢንዱስትሪዎች የግብአት ችግር እንዳይግጥማቸው ሃገር ውስጥ ያለውን እምቅ አቅም ለመጠቀም በመንግሥት ሰፊ ሥራ እየተሰራ ሲሆን በውጤቱም ተጨማሪ አሴት ያለውን የሃገር ውስጥ ምርት 60% በመቶ ለማድረስ እና የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት ትኩረት መደረጉን ከመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review