ጥናቶች እና የምርምር ስራዎች ሳይንሳዊና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ መሆን አንዳለባቸው የኦሮሞ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ገለፀ ።
የኢንስቲትዩቱ የምርምር ስራዎች ሳይንሳዊና በእውቀት የተመሰረቱ እንዲሆኑ እና የጥናት እና የምርምር ስራዎች ጥራት ላይ ያተኮረ ስልጠና ለዘርፉ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች በኦሮሞ ባህል ማዕከል እየተሰጠ ነው።
የሚካሄዱት ምርምሮች እና ጥናቶች ሳይንሳዊ እና በእውቀት ላይ የተመሰረቱ መሆን እንደሚገባቸው የኦሮሞ ጥናትና ምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ አስራት ገልጸዋል ።
ኢንስቲትዩቱ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ያተኮረ 73 ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ጥናቶች እና ምርምሮች እየተካሄዱ መሆኑን አቶ ዝናቡ ተናግረዋል ።
የምርምር ስራዎች በጋራ ትርክት ላይ የሚያተኩር እና በጋራ መቆም የሚያስችሉ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑንም ገልጸዋል ።
የሚካሄዱ ማንኛውም የምርመራ ስራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ የምርምር ስራዎች መሆን እንደሚገባቸው የተናገሩት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደራራ ከተማ (ረ/ፕ) ናቸው ።
የኦሮሞን ባህል ፣ ኪነ ጥበብ እና ማንኛውም የምርመራ እና የጥናት ውጤቶች በአለም አቀፍ ቋንቋ ለአለም አቅፍ ማህበረሰብ ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም ተናግረዋል ።
የምርምር ስራዎች ለአንድ ችግር መፍትሄ በማመላከት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳላቸዉ የገለፁት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋና ስነ- ፅሁፍ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ታደሰ ጃለታ ( ዶ/ር ) የምርምር ስራ በምርምር ሂደት በዉስጡ በርካታ ሳይንሳዊ ሂደቶችንና ግብዓቶችን ማካተት እንዳለበት ተናግረዋል።
በዳንኤል መላኩ