ጎጃም በረንዳ አካባቢ በአንድ ፎቶ ቤት ዉስጥ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

You are currently viewing ጎጃም በረንዳ አካባቢ በአንድ ፎቶ ቤት ዉስጥ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጁ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

AMN ጥቅምት 22/2018

ሀሰተኛ ሰነድ የሚያዘጋጁ ግለሰቦችን የተመለከተ መረጃ ከህብረተሰቡ የደረሰው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል፡፡

አበበ አሰፋ እና ፍቃዱ ሳሙኤል የተባሉት ተጠርጣሪዎች ሀሰተኛ ሰነዱን ሲያዘጋጁ የቆዩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ጎጀም በረንዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

ተጠርጣሪዎቹ በህጋዊ ንግድ ሽፋን ህገ-ወጥ ተግባር የሚፈፅሙ ስለመሆናቸው በምርመራው ሂደት ማወቅ ተችሏል።

ሃሰተኛ ሰነዶቹን የሚያዘጋጁት በአንድ ፎቶ ቤት ውስጥ እንደነበር ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

በፎቶ ቤቱ ውስጥ በህግ አግባብ በተደረገ ብርበራ በተለያዩ ሰዎች ስም የተዘጋጁ ሀሰተኛ መንጃ ፈቃዶች፣ ልዩ ልዩ የትምህርት ማስረጃዎች፣ የልደት ሰርተፍኬት፣ ሀሰተኛ ቲተርና ማህተሞች፣ የተለያዩ ተቋማት ሰነዶች እንዲሁም ሀሰተኛ ሰነዶቹን የሚያዘጋጁባቸው የተለያዩ ቁሳቁሶች ተይዘው ምርመራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review