ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ማንችስተር ዩናይትድ፦ ዩናይትድ አራተኛ ተከታታይ ድል ለማግኘት የሚያደርገው ጨዋታ

You are currently viewing ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ማንችስተር ዩናይትድ፦ ዩናይትድ አራተኛ ተከታታይ ድል ለማግኘት የሚያደርገው ጨዋታ

AMN-ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም

በውድድር ዓመቱ ሦስት አሰልጣኞችን የቀያየረው ኖቲንግሃም ፎረስት ማንችስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል።

10ኛ ሳምንት የሊግ መርሃግብሩን በሜዳው ሲቲ ግራውንድ የሚጫወተው ፎረስት ከዘጠኝ ጨዋታ አምስት ነጥብ ብቻ ይዞ 18ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

አዲሱ አሰልጣኝ ሾን ዳይች በዩሮፓ ሊግ ፖርቶን በማሸነፍ ቢጀምሩም በሊጉ በቦርንማውዝ ተሸንፈዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ በሩበን አሞሪም እየተመራ በሊጉ ስኬታማውን ጊዜ እያሳለፈ ይገኛል።

የ40 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታ አሸንፎ ነው ፎረስትን ለመግጠም የተዘጋጀው።

በታክቲኩ ረገድ መጠነኛ ለውጥ ማድረጉ እና አዲስ ፈራሚዎቹ ጥሩ ብቃት ማሳየታቸው ዩናይትድን አነቃቅቷል።

የዛሬው ጨዋታ ግን ቀላል አይሆንም ፤ ፎረስት በሦስት የመጨረሻ የሊግ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድን ማሸነፍ ችለዋል።

ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ላይ የሚከናወን ይሆናል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review