አርሰናል መሪነቱን ለማጠናከር በርንሌይን ይገጥማል

You are currently viewing አርሰናል መሪነቱን ለማጠናከር በርንሌይን ይገጥማል

AMN-ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 10ኛ ሳምንት የሊጉ መሪ አርሰናል በተርፍ ሙር በርንሌይን ይገጥማል።

መድፈኞቹ አሁን ላይ እያሳዩት በሚገኘው ብቃት ለዋንጫው ቀዳሚ ተገማች ሆነዋል።

በጥቅምት ወር በሁሉም ውድድር ያከናወኑትን ስድስት ጨዋታ ግብ ሳይቆጠርባቸው አሸንፈዋል።

በውድድር ዓመቱ ካደረጓቸው 14 ጨዋታዎች የተቆጠረባቸው የግብ ብዛት ሦስት ብቻ ነው።

በሁሉም የሜዳ ክፍል ጥንካሬውን እያሳየ የሚገኘው አርሰናል ዛሬም በርንሌይ ላይ ያስቀጥላል ተብሎ ይጠበቃል።

በርንሌይ ከአርሰናል ጋር ሲጫወት ጥሩ ክብረወሰን የለውም።

በስኮት ፓርከር የሚመራው ክለብ ከመጨረሻ 18 የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሙሉ ሦስት ነጥብ ይዞ የወጣው በአንዱ ብቻ ነው።

አርሰናል በአንፃሩ 13ቱን ጨዋታዎች አሸንፏል።

የዛሬ ጨዋታቸው ምሽት 12 ሰዓት ሲል ይጀመራል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review