ከጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ሁለተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።
“የወጣቶች ኦሎምፒክ ውድድር ለሀገር ማንሰራራት” የውድድሩ መሪ ሀሳብ ነው።
ውድድሩ በ20 የስፖርት ዓይነቶች ሲካሄድ የቆየ ሲሆን ሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተሳትፈውበታል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የወጣቶች ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እና በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ጨምሮ በተለያዩ ሜዳዎች ሲካሄድ ቆይቷል።
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ የወጣቶች ጨዋታዎች የተቋረጠውን የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታ በማስቀጠል ተተኪ ስፖርተኞችን ለማዘጋጀትና ለማብቃት ዓላማ ያደረገ የባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የወጣቶች ጨዋታው ለመጀመሪያ ጊዜ በዳካር በሚካሄደው የዓለም የወጣቶች ኦሎምፒክ የሚሳተፉ አትሌቶች የሚመረጡበትም ነው።
ጤናማ ማህበረሰብን መገንባት እና የዜጎችን የእርስ በእርስ ግንኙነት ማጠናከር ሌላኛው የውድድሩ ግብ መሆኑ ተገልጿል።
ሁለተኛው የኢትዮጵያ ወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሚደረግ የመዝጊያ ስነ ስርዓት እንደሚጠናቀቅ ሚኒስቴሩ አመልክቷል።