የሕግ የበላይነትን በዘላቂነት ለማስቀጠል አንድነታችንን እያጠናከርን ዛሬም እንደ ትናንቱ ታሪክ እየሰራን እንቀጥላለን ሲሉ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገለጹ

You are currently viewing የሕግ የበላይነትን በዘላቂነት ለማስቀጠል አንድነታችንን እያጠናከርን ዛሬም እንደ ትናንቱ ታሪክ እየሰራን እንቀጥላለን ሲሉ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ገለጹ

AMN ጥቅምት 22/ 2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ የሕግ የበላይነትን በዘላቂነት ለማስቀጠል አንድነታችንን አጠናክረን ማንኛውንም መስዋትነት እየከፈልን ዛሬም እንደ ትናንቱ ታሪክ እየሰራን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ ለመጀመሪያ ዙር የልዩ ፀረ ሽብር ኮማንዶ ሰልጣኞች እየተሰጠ ያለውን ስልጠና ጎብኝተዋል።

አሁን ላይ ልዩ ልዩ ፈታኝ የሆኑ ሙያዊ የስልጠና ውጣ ውረዶችን በማለፍ ላይ ያላችሁ የልዩ ፀረ ሽብር ኮማንዶ ሰልጣኞች እየወሰዳችሁ ያላችሁት ስልጠና ማንኛውም የአየር ፀባይና የመልክዓ ምድር አቀማመጥ ሁኔታ ሳይበግራችሁ በቀጣይ የሚሰጣችሁ ማንኛውንም ሀገራዊ ግዳጅ በብቃት ለመወጣት የሚያስችላችሁ በመሆኑ ስልጠናውን በተገቢው ማጠናቀቅ አለባችሁ በማለት የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ነፃነቷን አስከብራ ያለች እና ወደ ፊትም የምትኖር የሀገራችን ሰንደቅ ዓለማና የህዝቦቿ ክብር የሚጠብቅ እንዲሁም በህልውናዋ ጉዳይ ላይ ሊሰነዘር የሚችል ማንኛውንም ጥቃት በአስተማማኝ ሁኔታ መመከት የሚችል የልዩ ፀረ ሽብር ኃይል ኮማንዶ ባለቤት መሆኑንም ገልፀዋል።

ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል የብሔር ብሔረሰቦችን እኩልነት መብትና ግዴታን ለማረጋገጥና ሕገ- መንግስቱን ለማክበርና ለማስከበር ከማንኛውም ሐይማኖት፣ ከብሔርተኝነትና ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዳ የፖሊስ ኃይል በመሆን ሀገራችንን በዕውቀት፣ በደምና በላብ እንዲሁም እስከ ሕይወት መስዋዕትነት ዋጋ በመክፈል በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንዳለባቸው ሰልጣኞችን አሳስበዋል።

እስከአሁንም የተሰጠውን ግዳጆች ሁሉ በብቃት እየተወጣ ላለው ለልዩ ፀረ-ሽብር ኮማንዶ አመራርና አባላት ላቅ ያለ ምስጋና ማቅረባቸዉን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ለኤኤምኤን በላከዉ መረጃ አስታዉቋል

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review