አርሰናል አራተኛ የቻምፒየንስ ሊግ ድሉን ለማግኘት ከሜዳው ውጪ የቼኩን ክለብ ስላቪያ ፕራግን ይገጥማል።
የመጀመሪያ ሦስት ጨዋታዎችን ምንም ግብ ሳይቆጠርበት ያሸነፈው አርሰናል ዛሬም የማሸነፍ ግምት ተሰጥቶታል።
የሚካኤል አርቴታው ቡድን አሁን እያሳየ ያለው ወጥ ብቃት ደጋፊዎች በተስፋ እንዲሞሉ ያደረገ ሆኗል።
መድፈኞቹ በሁሉም ውድድሮች ያደረጓቸው የመጨረሻ ዘጠኝ ጨዋታዎችን አሸንፈዋል።
አርሰናል የዛሬ ተጋጣሚው ስላቪያ ፕራግን ሁለት ጊዜ ገጥሞ አንዱን ሲያሸንፍ በአንዱ አቻ ተለያይቷል።
ምሽት 2:45 ላይ በሚጀምረው ጨዋታ አጥቂው ቪክቶር ዮኬሬሽ በጉዳት እንደማይሳተፍ ሚካኤል አርቴታ አረጋግጧል።
በሌሎች ጨዋታዎች አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሴንት ጂልዋስ ፣ ቶተንሃም ከ ኮፐንሃገን ፣ ጁቬንቱስ ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን ፣ ኦሎምፒያኮስ ከ ፒ ኤስ ቪ አይንዶቨን እንዲሁም ቦዶ ከ ሞናኮ ምሽት 5 ሰዓት ይጫወታሉ።
ናፖሊ በሜዳው ፍራንክፈርትን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ምሽት 2:45 ሲል ይጀምራል።
በሸዋንግዛው ግርማ