የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የንግድ አሰራርን የበለጠ ለማሻሻል እንደሚሰራ ገለጸ

You are currently viewing የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የንግድ አሰራርን የበለጠ ለማሻሻል እንደሚሰራ ገለጸ

AMN- ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

በአውሮፓ ህብረት-ኢትዮጵያ የንግድ ፎረም ላይ የኢትዮጵያን የንግድ ከባቢ የሚያሻሽሉ እና ቀጣይነት ያለውን ኢንቨስትመንት የሚስቡ ማሻሻያዎችን የበለጠ ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አመላክቷል።

ተወዳዳሪነትን እና የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማስፋት የሚያግዙ ዘመናዊ አሰራሮች እና አገልግሎቶችን ማስተዋውቅ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል መሆናቸው በዚሁ ወቅት ተጠቅሷል።

አሰራር እና ደንቦችን ማቀላጠፍ፣ ግልጽነትን ማሳደግ እንዲሁም የመንግሥትና የግል ዘርፍ አጋርነትን ለማጠናከር እየተወሰዱ ያሉት እርምጃዎች ላይ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ማብራሪያ ሰጥቷል።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የንግድ አካባቢ ለማሻሻል በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸው፤

ከዚህ የተሻለ ለስራ ፈጠራ እና ኢንቨስትመንት የተመቸ ሁኔታ ለመፍጠር መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኘም ነው የጠቆሙት።

የጀርመን ልማት ትብብር (ጂ አይ ዜድ)፣ የንግድ ሥራዎችን የሚያደናቅፉ ሁኔታዎች ለመቅረፍ እና ማሻሻያዎችን ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት የወሰዳቸውን እርምጃዎች አድንቋል።

የእነዚህን ማሻሻያዎች ዘላቂነት ለማረጋገጥም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት ለመስራት ያለውን ፍላጎት ድርጅቱ አንጸባርቋል።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር የኢኮኖሚ አማካሪ በበኩላቸው፤ በኢንቨስትመንት ከባቢ ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ ተዋናዮች መካከል ቀጣይነት ያለው ተሳትፎን ለማሳደግ የጋራ የሥራ ቡድን መቋቋሙ ተምሳሌታዊ ተግባር ነው ብለዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review