ወጣቶች ከጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት በመሸጋገር ከራሳቸው አልፎ ለትውልድና ለሀገር ለመትረፍ በትብብርና በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል

You are currently viewing ወጣቶች ከጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት በመሸጋገር ከራሳቸው አልፎ ለትውልድና ለሀገር ለመትረፍ በትብብርና በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል

AMN ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም

ወጣቶች ከጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት በመሸጋገር ከራሳቸው አልፎ ለትውልድና ለሀገር ለመትረፍ በትብብርና በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸዉ ተገለጸ፡፡

አብሮ መስራት የተነጣጠለ አቅምን ወደ ጋራ አቅም ከፍ በማድረግ፣ ጊዜን እና ጉልበትን በመቆጠብ ብሎም ስራን በጊዜው በማከናወን ውጤታማ መሆን እንደሚያስችል የስነጽሁፍ እና የማህበረሰብ አጥኚው መሐመድ አሊ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ወጣቶች ከጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት በመሸጋገር ከራሳቸው አልፎ ለትውልድና ለሀገር ለመትረፍ በትብብርና በቅንጅት መስራት ይገባል፡፡

ሰው አቅሙ በፈቀደው መጠንና እንደ ዝንባሌው ሊሰራ ይገባል ያሉት ዶ/ር መሐመድ፤ በርትቶ በመስራት ድህነትን ታሪክ ለማድረግ ከዚህ ዘመን ወጣት ብዙ እንደሚጠበቅ ምክረ-ኃሳባቸውን ሰጥተዋል።

ማህበረሰቡ ውስጥ በሥነ ግጥም ሰነፍ እና ታታሪ የሚገለጽበት አንድምታ እንዳለ ያስታወሱት ዶ/ር መሐመድ፣ ከሚቀበል እጅ የሚሰጥ እጅ ይበልጣል ተብለዉ የሚነገሩ አባባሎች የራሳቸው የሆነ መልዕክት ያስተላልፋሉ ብለዋል።

እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ አስተዳደር የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል የተለያዩ ኘሮግራሞች ተቀርፀው እየተተገበሩ ሲሆን፤ በተለይ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ የሚገኘው የሥራ ዕድል ፈጠራ ዜጐችን በየደረጃው ተጠቃሚ ማድረግ እየተቻለ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review