ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ የዓለምን ህግ የጣሰ የሞራል ልዕልናንም የሚፈታተን ህዝብን ያገለለ የጫካ ውል ነው

You are currently viewing ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ የዓለምን ህግ የጣሰ የሞራል ልዕልናንም የሚፈታተን ህዝብን ያገለለ የጫካ ውል ነው

AMN- ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም

የባህር በር ከማጣታችን በላይ ያጣንበት መንገድ የዓለምን ህግ የጣሰ፣ የሞራል ልዕልናንም የሚፈታተን፣ ህዝብን ያገለለ እና የወቅቱን ፓርላማ ውሳኔ የዘነጋ የግለሰቦች የጫካ ዉል ነው ሲሉ የታሪክ ምሁር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር አደም ካሚል ተናገሩ፡፡

ህዝብ ያልመከረበት እና ያልዘከረበት የወቅቱ ፓርላማም ውሳኔ ያላሳለፈበት የግለሰቦች የጫካ ስምምነት የሀገርን ላንቃ ዘግቶ ዓመታቶች መቆጠራቸውንም ነው ምሁሩ የገለጹት፡፡

የታሪክ ድርሳናት ሲገለጡ ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ንግስት ነበረች፤ በቀይ ባህር የአፋር ግመሎች ውሀ ተጎንጭተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የንግድ መርከቦች ያለ ከልካይ ተንጎማለዋል፤ ወዲህ ደግሞ የኢትዮጵያ የባህር ሀይል የበርካቶች ትዝታ ነዉ፡፡

በግለሰቦች ውል ሀገር ባህር በሯ ሲቆለፍባት የአፋር ግመሎች ልክ እንደ ሰዉ አንብተዋል፤ የንግድ መርከቦች ተገቱ የባህር ኃይሉም ተበተነ፡፡

የታሪክ ምሁር እና ተመራማሪዉ ፕሮፌሰር አደም ካሚል፣ የባህር በር ከማጣታችን በላይ ያጣንበት መንገድ የዓለምን ህግ የጣሰ የሞራል ልዕልናንም የሚፈታተን ህዝብን ያገለለ የወቅቱን ፓርላማ ውሳኔ የዘነጋ የግለሰቦች የጫካ ውል መሆኑን ያነሳሉ፡፡

ቀይ ባህር እና ኢትዮጵያ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች እንደነበሩ የሚያነሱት የታሪክ ምሁር እና ተመራማሪው፣ ባለፉት ጊዚያት ህዝብን እንደ እግር እሳት እያቃጠለ ዛሬ ስለመደረሱ ይናገራሉ፡፡

የቀይ ባህርን ጉዳይ ከዚህ በፊት በነበረው ስርዓት ማንሳት አንድም ነውር ወይም ሳንሱር ተደርጎ ይወሰድ እንደነበር የሚያነሱት የታሪክ ምሁሩ፣ ያ ሁኔታ አሁን ላይ ያከተመለት ጉዳይ ሆኗል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ታሪክ ሲገለጥ የኢትዮጵያዊያንም ማንነት ሲመዘን አንድም ፍትህ በሌላ መልኩ ሰላም ወዳድነት ገፋ ሲልም ለነፃነት መዋደቅ ነው የሚሉት የታሪክ ምሁሩ፣ ዛሬም እነዚህ ትውፊቶች አልነጠፉም ባይ ናቸዉ፡፡

የኢትዮጵያን የመልማት ፍላጎት እና በጫካ ውል ያለፈችባቸዉን የግፍ ዓመታት ለዓለም ማሳወቅ ኢትዮጵያዊያኑም የውስጥ አብሮነታቸውን በማጥበቅ፣ ለተጠቃሚነታቸው በጋራ መትመም እንደሚጠበቅባቸው ምክረ ሀሳባቸዉን ለግሰዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review