በመዲናዋ ህግን ለማስከበር በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ወንጀል እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል

You are currently viewing በመዲናዋ ህግን ለማስከበር በተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ወንጀል እንዲቀንስ ማድረግ ተችሏል

AMN – ጥቅምት 27 /2018 ዓ.ም

በመዲናዋ ህግን ለማስከበር በወንጀል ፈፃሚዎች እና በተባባሪዎቻቸው ላይ በተወሰዱ እርምጃዎች ወንጀል እንዲቀንስ ማድረግ መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የ2018 ዓ.ም የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈፃፀምን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ገምግሟል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጌቱ አርጋው እንደገለጹት፣ በወንጀል መከላከልና ምርመራ ዘርፍ በ1ኛው ሩብ አመት በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን አንስተው፣ይህም በጋራ ስራ የመጣ ውጤት መሆኑን ተናግረዋል።

መዲናዋ ያስተናገደቻቸው የመስቀል ደመራ እንዲሁም የኢሬቻ በዓላትን ጨምሮ አህጉራዊና አለም አቀፋዊ መድረኮች፣ ኢትዮጵያዊነትን በተላበሰ መስተንግዶ ባህላዊና ሀይማኖታዊ እሴታቸውን ጠብቀው መጠናቀቃቸውን የተናገሩት ኮሚሽነሩ፣ ለዚህም የመዲናዋ ነዋሪዎች ያበረከቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

ህግን በማስከበር ሂደት ውስጥ በተከናወኑ ስራዎች ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ እንዲሁም ተባባሪዎቻቸው ላይ በተወሰዱ እርምጃዎች ወንጀል እንዲቀንስ ማድረግ ስለመቻሉ ጠቁመዋል።

የትራፊክ አደጋን መቀነስ፣ የአመራሩንና አባሉን አቅም ለማሳደግ እንዲሁም በሀገራዊ ሁነቶች ዙሪያ ግንዛቤዎች እንዲኖሩ ለማስቻል የተሰሩ ስራዎች በርካታ ውጤቶችን ማምጣታቸውን ገልፀው፣ በቀጣይም የመዲናዋን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል በትብብር መስራት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል።

በሩብ አመቱ የአፈፃፀም ግምገማም የክፍለ ከተማ የስራ ክንውኖች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።

በራሄል አበበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review