የእድሳት ሥራው የቤተመንግሥቱን የግንባታ መዋቅር መጠገን፣ የእግር መንገዶችን ማሻሻል፣ ቁልፍ የሆኑ ሕንፃዎችን ከዝግባ እና ዋንዛ በባሕላዊ ቁሳቁሶችን ተጠቅሞ በማደስ የስፍራውን ግለ ወጥ መልክ እና ባሕርይ ለመጠበቅ ተሰርቷል።

ለጎብኝዎች ምቾት የተሰናዱ አገልግሎት መስጫዎችም ትርጉም ባለው ደረጃ ተሻሽለዋል። አዲስ የቱሪስት ማዕከልም ተከፍቷል። ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ የተሻሻሉ የመብራት እና የደኅንነት ሥርዓቶችም ተሰናድተዋል። እንደ አፄ ፋሲል፣ አፄ ቀዳማዊ ዮሃንስ እና አፄ ቀዳማዊ ኢያሱ አቢያተ መንግሥት ብሎም ድልድዮች፣ መታጠቢያ ሥፍራዎች፣ ታሪካዊ በሮች ወዘተ በጥንቃቄ ታድሰዋል።

በተጨማሪም ከ40,000 ስኴር ሜትር በላይ የአካባቢው ምድር የማስዋብ ሥራ ተሰርቷል። ይኸም ለጎብኝዎች ይበልጥ ሳቢ የሆነ ከባቢ ፈጥሯል። አጠቃላይ የእድሳት ሥራው ከአንድ አመት በታች የፈጀ ሲሆን የዚህን አስደናቂ የታሪክ እና የባሕል ሥፍራ ለረዥም ጊዜ ጠብቆ በሚያቆይ አኳኋን ተከናውኗል። – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት