በስልጠና ላይ የሚገኙ የፌደራል : የከተማ እና የተለያዩ ክልሎች ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ በክላስተር በመልማት ላይ የሚገኝ የፓፓያ ማሳን ጎብኝተዋል።

በክላስተር እየለማ የሚገኘዉ የፓፓያ ዝርያ በዘጠኝ ወራት ዉስጥ ምርት እንደሚሰጥ ሲሆን ልዩ ጣዕም ያለዉና በገበያ ላይ ተፈላጊ መሆኑ ተገልጿል።
ከአንድ የፓፓያ ተክል እስከ አንድ ኩንታል የሚደርስ ምርት እንደሚገኝ ከምስራቅ ሸዋ ዞን ግብርና ጽ/ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።
በጉብኝቱ ላይ የታደሙ አመራሮችም ያገኙትን ተሞክሮ በአካባቢያቸዉ ለማስፋፋት የሚሰሩ መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል።