የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን ተበሠረ

You are currently viewing የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን ተበሠረ

‎AMN -ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን መበሰሩን ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ የፋሲል ግንብ ለአራት መቶ ዓመታት ያህል የሚንከባከበው አጥቶ የእርጅና እድሜው ላይ ደርሶ ሞቱን ነበር የሚጠብቀው ብለዋል።

ሆኖም ግን በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶር)፣ አመራርነትና ክትትል እንደ ንሥር ታድሶ ተነስቷል ብለዋል፡፡

ከአዞዞ እስከ ፒያሳ ያለው የጎንደር መንገድ ግራና ቀኙ እየተስተካከለ እና እያማረ ዳግም እየተወለደ ነው። ያውም ውበት፣ ጥቅምና ምቾት ጨምሮ።

ተጀምሮ ያለማለቅና ቆሞ የመቅረት መተረቻ የሆነው መገጭ ዛሬ ታሪኩ ተቀየረ። ወድቆ የመነሣት፣ ደክሞ የመበርታት ምሳሌ ሆነ። ወንዙ ተቀለበሰ። አንዱን ወሳኝ ምእራፍ ተሻገረ።

እነሆ የጎንደር ሁለተኛው የሥልጣኔ ዘመን በዚህ ሰሞን ተበሠረ ሲሉም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review