የብልጽግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራር ስልጠና የአባላቱን አቅም የሚገነቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።
የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ስልጠና በኢትዮጵያ የግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት መሰረታዊ የኢኮኖሚ ዘርፎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡
የፓርቲዉ አመራሮች ከስልጠናዉ በተጓዳኝ በአዲስ አበባ ከተማ የመስክ ጉብኝት እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
አመራሮቹ መነሻቸዉን ከአራዳ ፓርክ እና ከሳይንስ ሙዚየም በማድረግ በአራት ቡድን በተለያዩ አቅጣጫዎች በመዲናዋ የተከናወኑ የተለያዩ የልማት ስራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል፡፡
በስልጠናዉ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙት አመራሮቹ በአዲስ አበባ ከተማ የተገነቡ የተለያዩ የልማት ስራዎችን የኮሪደርና ወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎችን፤ ፓርኮችን፤ የገበያ ማዕከላትን፤ ሙዚየሞችንና ሌሎች የልማት ስራዎችን መጎብኘት ጀምረዋል፡፡
በወንድማገኝ አሰፋ