ተመራጭ የምግብ ዓይነት እየሆነ የመጣዉ እንጉዳይ ወይም መሽሩም

You are currently viewing ተመራጭ የምግብ ዓይነት እየሆነ የመጣዉ እንጉዳይ ወይም መሽሩም

AMN – ጥቅምት 29/2018 ዓ.ም

እንጉዳይ በትንሽ ቦታና በቀላል ካፒታል የሚመረት መሆኑን እና ከፍተኛ ገቢ የሚያስገኝ ምርት ነዉ፡፡

ወይዘሮ በላይነሽ በየነ ፣ የበላይነሽ ሙሉ እመቤትና ጓደኞቿ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር አባል ናቸው ፣ የማህበሩ አባላት እንጉዳይን በትንሽ ቦታ በማምረት ትርፋማና ተጠቃሚ መሆን እንደ ቻሉ ተናግረዋል።

ሌላኛዋ የማህበሩ አባል ወይዘሮ ትግስት ታደስ እንጉዳይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሚደርስ ምርት መሆኑን በመግለጽ አሁን ላይ ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እያቀረቡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ማህበሩ በቀጣይ ምርቶቹን በጥራትና በብዛት በማምረት ከሀገር ውስጥ ገበያ ተጨማሪ ለውጭ ገበያ ለማቅረብም እቅድ እንዳላቸዉ ወይዘሮ ትግስት ታደሰ ተናግረዋል፡፡

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በዘርፉ ለተሰማሩ አራት ማህበራትና ሁለት ግለሰቦች ስልጠናና የተለያዩ የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ወደ ስራ እንዲገቡ ማስቻሉን የገለጹት ደግሞ በፋርም አፍሪካ ድርጅት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 የከተማ ግብርና አስተባባሪ አቶ በቀለ ኩማ ናቸው ።

በከተማ ግብርና የችግኝ ብዜት ማእከል ስልጠና ከወሰዱት ውስጥ ሁለቱ ወደ ስራ መግባታቸውን አስተባባሪው ለኤ ኤም ኤን ዲጂታል ሚዲያ ተናግረዋል።

በከተማ አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ 1ሺህ ለሚደርሱ በዘርፉ ለተሰማሩ ማህበራትና ግለሰቦች ስልጠናን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ተግባር እየተከናወነ ነው ያሉት ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ኮሚሽን የከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያ ብዜት ማእከል ስራ አስኪያጅ አቶ አብደታ ደሜ ናቸዉ፡፡ የገበያ ፍላጎቱ ከፍተኛ ቢሆንም አቅርቦቱ አነስተኛ መሆኑንም አብራርተዋል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review