የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸዉ እና ከሕግና መመሪያ ውጭ በሚሰሩ ጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ላይ እርምጃ ይወሰዳል

You are currently viewing የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸዉ እና ከሕግና መመሪያ ውጭ በሚሰሩ ጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ላይ እርምጃ ይወሰዳል

AMN – ጥቅምት 28/2018 ዓ.ም

የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸዉ እና ከሕግና መመሪያ ውጭ በሚሰሩ ጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳዳር ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮዉ፣ በከተማዋ ከሚገኙ ጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ጋር በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ምክክር እያደረገ ይገኛል፡፡

የመዲናዋ ነዋሪዎች ንብረታችውን በሚያንቀሳቅሱበት ወቅት አላስፈላጊ ዋጋ በጫኝ እና አውራጆች ሲጠየቁ፣ ለእንግልትና ምሬት ሲዳረጉ እንደነበር ይታወሳል::

ይህን ችግር ለመቅረፍም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላም እና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አገልግሎቱ በሕግ እና ሥርዓት እንዲመራ ህግና ደንብ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል::

የቢሮው ምክትል ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር የጫኝ እና አዉራጅ ህግና ደንብ ወጥቶ ወደ ስራ ከተገባ በኋላ፣ ከዚህ ቀደም ህዝቡ ሲያነሳቸው የነበሩ ቅሬታዎች እና እንግልቶች መቀነሳቸውን ተናግረዋል::

ሕግና እና ደንብን አክብረዉ የሚሰሩ በአርአያነት የሚጠቀሱ ጫኝና አዉራጆች መፈጠራቸዉን የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ፣ ሆኖም ግን የስነ ምግባር ጉድለት ያለባቸዉ እና አሁንም ከሕግ እና መመሪያ ውጭ የሚሰሩ ጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት መኖራቸዉንም ተናግረዋል::

በህዝቡ ዘንድ ቅሬታ በሚያሰነሱ እና ከሕግ እና መመሪያ ውጭ በሚሰሩ ጫኝ እና አዉራጅ ማህበራት ላይ እርምጃ እንደሚወስድም ተመላክቷል::

በቴዎድሮስ ይሳ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review