በመዲናዋ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤታማ መሆናቸዉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

You are currently viewing በመዲናዋ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤታማ መሆናቸዉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ

AMN ጥቅምት 29/2018

በአዲስ አበባ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና የአባላቱን አቅም የሚገነቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሰሞኑን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ስልጠና በሀገሪቷ መሰረታዊ የኢኮኖሚ ዘርፎች በግብርና፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ዘርፎች ላይ ያተኮረ እንደነበር ተገልጿል፡፡

የፓርቲው ከፍተኛ አመራር አባላት በአዲስ አበባ የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማት፣ የቤት ልማት እና አቅርቦት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በመዲናዋ ህዝብን በማሳተፍ የተከናወኑ የልማት ተግባራት ውጤት አምጥተዋል፡፡

በዚህም አዲስ አበባን በአፍሪካ ተጠቃሽ ያደረገ ውጤቶች የተገኘበት ነው ብለዋል።

በቤት ልማትና አቅርቦት ላይ የግሉን ዘርፍ በማሳተፍ የተከናወኑ ስራዎች አቅርቦቱን ለማሳደግ ማስቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

በተሰሩ ስራዎች በርካታ አቅመ ደካሞች ቤት ማግኘታቸውን የገለጹት ከንቲባዋ፤ በትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብር ውጤት መገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡

በመዲናዋ ህጻናትንና ወጣቶችን ታሳቢ ያደረጉ የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች ፥ መፍጠርና መፍጠን መርህን በመከተል ርብርብ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review