አዲስ አበባ አሁን ላይ እንደ ገና ተወልዳለች ሲሉ የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ኤልያስ ዑመታ ተናግረዋል ፡፡
አቶ ኤሊያስ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በጎበኙበት ወቅት ነው ፡፡
አዲስ አበባ ላይ የተመዘገበው ለውጥ ከመደመር እሳቤ የመነጨና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ በመነሻ በማድረግ በለወጡ በተሻሻሉ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች መሆኑን ያነሱት አቶ ኤሊያስ ከባለፈው ጥሩውን ወስደን ዛሬ ላይ ዘመኑ የደረሰበትን በማቀናጀት የተሰራው ስራ መሬት የያዘ ነው ሲሉ ገልፀዋል ፡፡
አሁን ላይ ከተማና ገጠሩን የሚያስተሳስሩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ያነሱት አቶ ኤሊያስ የአርሶ አደሩን ምርት ከከተማው ጋር የሚያስተሳስሩ የገበያ ማዕከላትም በአዲስ አበባ መኖሩ በተሳለጠ መልኩ ተጠቃሚው መርቶችን እንዲያገኝ ያደርጋል ነው ያሉት ፡፡
በከተማዋ የተሰሩ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ከዚህ ቀደም የነበረውን የወንዞች ታሪክ የቀየረ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አዲስ አበባ የሚለው ስያሜ ቀድሞ ለስም መጠሪያ ነበር አሁን ግን በተግባር ስመ ጥር ከተማ የሚያደርጋትን ውበት በመጎናፀፍ ስሟን የሆነች ከተማ ሆናለች ሲሉ ነው አቶ ኤሊያስ የተናገሩት ፡፡
በያለው ጌታነህ