በየቀኑ ከ8 እሰከ 10 ኪሎ ሜትር የሚሮጡት የቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰርን ቬንገር

You are currently viewing በየቀኑ ከ8 እሰከ 10 ኪሎ ሜትር የሚሮጡት የቀድሞ የአርሰናል አሰልጣኝ አርሰርን ቬንገር

AMN-ጥቅምት 30/2018 ዓ.ም

ፈረንሳዊው አሰልጣኝ አርሰን ቬንገር በአርሰናል በቆዩባቸው ሃያ ሁለት አመታት በርካታ ዋንጫዎችን አንስተዋል።

አርሰናል አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ ዋንጫን ያነሳበት እኤአ የ2003/04 የውድድር ዘመን ጨምሮ ሶሰት የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫ ፣ ሰባት ኤፍኤ ካፕ እና ሰባት የኮሚኒቲ ሺልድ ዋንጫ ማንሳት ችለዋል።

የራሳቸውን የእግር ኳስ ፍልስፍና እንደሚከተሉ የሚነገርላቸው አርሰን ቨንገር በማለዳ ከቤታቸው በመውጣት በሩጫ ቀናቸውን የመጀመር ልምድ አላቸው።

በፈረንጆቹ ሚሊኒየም መባቻ የጀመሩት የመሮጥ ልማድ በአዛውንትነት ዕድሜያቸውም አልተቋረጠም።

ላለፉት 24 ዓመታት በየቀኑ ከ ስምንት እስከ 10 ኪሎ ሜትር መሮጥ የዘወትር ተግባራቸው አድርገውታል።

አርሰን ቬንገር “ሩጫ ስሮጥ በተሻለ መልኩ ቀኔን እንድጀምር እና በተለየ መልኩ እንዳስብ ያደርገኛል ” ሲሉ ስለ ልማዳቸው ተናግረዋል።

የአእምሮ ጤናቸውን ጨምሮ የአካል ጥንካሬያቸውን እንደጨመረ የሚናገሩት አርሰን ቬንገር በጎዳናዎች ላይ መሮጥ የማይችሉበት ሁኔታ ቢፈጠር በጂም ውሰጥ እንደሚሮጡ ገልፀዋል።

አርሰን ቬንገር ዛሬም ከእግር ኳሱ ሳይርቁ በፊፋ የእግርኳስ ልማት ላይ እየሰሩ ይገኛሉ።

በጃዕፈር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review