ሌላኛው የመዲናዋ መልክ – የብስክሌት ሰረገላ አገልግሎት

You are currently viewing ሌላኛው የመዲናዋ መልክ – የብስክሌት ሰረገላ አገልግሎት

AMN- ህዳር 01/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ የልማት እና ከተማዋን የማስዋብ ሥራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ፡፡

እነዚህ የተሰሩ የልማት ሥራዎች ለከተማዋ ውበትን ከማጎናፀፍና ለከተማዋ ነዋሪዎች የመዝናኛ አማራጭ ከመሆን ባለፈ የሥራ ዕድልም እየፈጠሩ ናቸው፡፡

ናሆም ደረሰ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ነው ፣ ለየት ባለና ባልተለመደ የሥራ መስክ የተሰማራ የሥራ ፈጣሪ ወጣት ነው፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ የብስክሌት ሰረገላ አገልግሎት በመመልከቱ እርሱም ሰረገላ ለመስራት እንደተነሳሳ ከኤ ኤም ኤን መዝናኛ ጋር ባደረገው ቆይታ አጫውቶናል ፡፡

የብስክሌት ሰረገላው አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ ሰዎች አንዳንዴ ፍርሃት ያድርባቸዋል ያለው ወጣቱ፤ ነገር ግን አገልግሎቱ አዝናኝ መሆኑን ነው የገለፀው::

በዋናነት ለመዝናኛነት እና ለጎብኚዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ የተናገረው ናሆም ፣ ተገልጋዮችም በአገልግሎቱ ደስተኛ መሆናቸውን ገልጿል፡፡

የብስክሌት ሰረገላ ሥራው አሁን ላይ እየተለመደለት በመምጣቱ፣ በቀጣይ በተለያዩ የከተማዋ አካባቢዎችም አገልግሎቱን ለማስፋት ፍላጎት እንዳለው ገልጿል፡፡

የብስክሌት ሰረገላ አገልግሎት ከእሁድ እስከ እሁድ ምሽት ከ11፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚሰጥም ነው የተናገረው፡፡

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review