በሮቦት የታገዘዉና በዓለም የመጀመሪያዉ የሆነዉ የስትሮክ ቀዶ ጥገና ተካሄደ

You are currently viewing በሮቦት የታገዘዉና በዓለም የመጀመሪያዉ የሆነዉ የስትሮክ ቀዶ ጥገና ተካሄደ

AMN- ህዳር 2/2018 ዓ.ም

የስኮትላንድ እና የአሜሪካ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች በሮቦት በመታገዝ በዓለም የመጀመሪያው የተባለለትን የስትሮክ ቀዶ ጥገና በተሳካ ሁኔታ አካሂደዋል፡፡

የስኮትላንድ ዱንዲ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር አይሪስ ግሩንዋልድ፣ በሰው አስከሬን ላይ ከስትሮክ በኋላ የሚከሰት የደም መርጋትን የማስወገድ ስኬታማ ሥራ ማካሄዳቸውን ተናግረዋል።

ከሰዓታት በኋላ በፍሎሪዳ የሚገኙት የነርቭ ቀዶ ጥገና ሐኪም ሪካርዶ ሃኔል፣ ከ6 ሺህ 400 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት ላይ ሆነው፣ ቴክኖሎጂውን በመጠቀም በዱንዲ የመጀመሪያው የትራንስ አትላንቲክ የቀዶ ጥገና ህክምናን አካሂደዋል።

የሕክምና ቡድኑ ቴክኖሎጂው በታማሚዎች ላይ እንዲተገበር ፍቃድ የሚያገኝ ከሆነ ጨዋታ ቀያሪ እንደሚሆን ነው የገለጸው።

በእስፔሻሊስት ሕክምናን ለማግኘት የሚፈጠር መዘግየት የማገገም እድልን ሊጎዳ እንደሚችል የገለጹት የሕክምና ባለሙያዎቹ፣ ይህ ቴክኖሎጂ የስትሮክ ሕክምናን ሊለውጥ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

የዱንዲ ዩኒቨርሲቲ የዓለም አቀፍ ስትሮክ ሕክምና ፌዴሬሽን ጥምረት የሥልጠና ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ነዉ።

ይህ ዓይነት ክስተት ከዚህ ቀደም እንደ ሳይንስ ልብወለድ ይታይ ነበር ያሉት ፕሮፌሰር ግሩንዋልድ፣ እያንዳንዱ ሂደት በእውነተኛ የሰው አካል ላይ ማከናወን እንደሚቻል ያሳየንበት ነው ሲሉም መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በታምራት ቢሻው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review