‎የሰሜን ሸዋ ዞን በኢንዱስትሪ ልማት ማበብ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ግዙፍ ተደማሪ አቅም ነው

You are currently viewing ‎የሰሜን ሸዋ ዞን በኢንዱስትሪ ልማት ማበብ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ግዙፍ ተደማሪ አቅም ነው

AMN – ህዳር 02/2018 ዓ.ም

‎የሰሜን ሸዋ ዞን በኢንዱስትሪ ልማት ማበብ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት ግዙፍ ተደማሪ አቅም መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለፁ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ በሰሜን ሸዋ ዞን የሚገኙትን የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርክ፤ የሴራሚክ ፋብሪካ እና የፐልፕ የወረቀት ፋብሪካዎችን ተመልክተናል ብለዋል፡፡

እነዚህ ግዙፍ ፋብሪካዎች በኢንዱስትሪ ዘርፍ የጀመርነው ሃገራዊ ሪፎርም እና ትግበራ ውጤት እየታየበት ለመሆኑ ህያው ምስክሮች ናቸው።

ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት የያዘችው የአምራች ዘርፍ በባህሪው የሃብት ብዜት እና የዘርፎችን ትስስር የሚፈጥር መሆኑንም ገልፀዋል።

በሰሜን ሸዋ ዞን የተመለከትናቸው ፋብሪካዎች አምራች በመሆናቸው አዲስ ሃብትን ወደ ኢኮኖሚው ይደምራሉ፡፡ በዘርፎች ትስስርም የአንዱ ምርት ለሌላው ግብአት የሚሆንና በተለይ በስራ እድል ፈጠራ እና የውጭ ምንዛሬን በማዳኑ በኩል ትልቅ ሚናን የሚወጡ ናቸው ብለዋል፡፡

ሰላም እና ትጋት ካለ ፋብሪካዎች ለልማት፤ ዜጎች ለለውጥ ሃገርም ወደ ዘላቂ ብልጽግና እንደምትራመድ የሰሜን ሸዋ ዞን ማሳያ ናት ሲሉም ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review