20ኛዉን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች በዓል ለማክበር የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቃቸዉን የፌደሬሽን ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
በበዓሉ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ የፌደሬሽን ምክር ቤት መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በፌዴሬሽን ምክር ቤት የመንግስታት ግንኙነት፣ የዲሞክራሲ አንድነት እና የህገ መንግስት አስተምህሮ ቋሚ ኮሚቴ ፀሀፊ ባንችይርጋ መለሰ፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የህዝብን መተዋወቅ በማላቅ ለአንድ ሀገር ይሰሩ ዘንድ መንደርደሪያ የሚሆን ነዉ ብለዋል፡፡
በዓሉ የሀገር የቱሪዝም ሀብት የሚጎላበት ለሀገር ዉስጥ እና ለባህር ማዶ ጎብኝዎችም ያሉ ገፀ በረከቶች የሚታይበት ስለመሆኑም ተነግሯል፡፡
የብሄር ብሄረሰቦች ቀን የሀገርን ኢኮኖሚ የሚገነባ፤ ፀጋዎችንም የሚያስተዋዉቅ ነዉ ያሉት ባንችይርጋ መለሰ፤ በማህበራዊ ዘርፍም የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር ነዉ ብለዋል፡፡
በዓሉ ከህዳር 25 እስከ 29 በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በድምቀት እንደሚከበር ተነግሯል፡፡
በተመስገን ይመር