ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደብረ ብርሃን ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ፤ የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻዎችን መጎብኘታቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በደብረ ብርሃን ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ፤ የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻዎችን መጎብኘታቸዉን ገለጹ

AMN ህዳር 3/2018

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ከተማ በነበረን ቆይታ የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻዎችን ተመልክተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

መፍጠር፣ መፍጠን እና በጥራት መሥራት የሁልጊዜም የስራ መመሪያችን ሊሆን ይገባል፡፡

በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ከተማ በነበረን ቆይታ የመኪና መገጣጠሚያ እንዲሁም የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻዎችን ተመልክተናል።

በቆይታችን ያየናቸው ፋብሪካዎች የሀገር ውስጥ ግብዓትን በመጠቀምና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬን እያዳኑ ነው፡፡

ከብየዳ ጀምሮ ትላልቅ የኤሌትሪክ አውቶቡሶችን እየገጣጠመ የሚገኘው የፊቤላ ኢንዱስትሪያል መኪና መገጠሚያ በቀን 12 መኪና ማምረት በሚያስችል አቅም አለው፡፡ መገጣጠሚያው በቅርቡ ያስጀመረው አዲስ የቀለም መቀቢያ በርካታ ቀናትን ይወስዱ የነበሩ ስራዎችን በሰዓታት ለማከናወን አስችሏል ብለዋል፡፡

በአንድ ቀን 450 ሺህ ጠርሙስ የሚያመርተው ዴዴ ቦትል የብርጭቆና የጠርሙስ ማምረቻ ደግሞ 86 በመቶ የሚሆነውን ግብዓት ከሀገር ውስጥ ተጠቅሞ ለበርካታ የመጠጥ እና የመድሃኒት ፋብሪካዎች ጥቅም የሚሰጡ ጠርሙሶች ያመርታል፡፡

በኢንዱስትሪዎቹ የተመለከትናቸው አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴዎች በየዘርፉ በጥራትና በፍጥነት በመትጋት የምናልመውን እድገት በአጠረ ጊዜ እንደምናሳካ የሚያሳዩ ናቸው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review