ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል

You are currently viewing ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል

AMN- ህዳር 03/2018 ዓ.ም

ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወይዘሮ ቆንጅት ደበላ ተናገሩ፡፡

ቢሮው በዓለም ለ34ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው 16ቱ የፀረ-ፆታዊ ጥቃት የንቅናቄ ቀናትን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ፆታዊ ጥቃትን ሁሉም ሰው ሊፀየፈው እንደሚገባ ያነሱት የቢሮ ሀላፊዋ፣ ወንዶች የሴቷ ጠባቂ እንጂ ጥቃት ፈፃሚ ሊሆኑ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።

መጪው ትውልድ ፆታዊ ጥቃትን እንዲፀየፍ፣ ሁሉም የበኩሉን ሚና ሊወጣ ይገባል ሲሉም የቢሮ ሀላፊዋ ተናግረዋል፡፡

ቢሮው፤ በሴቶች እና ህፃናት ላይ ሊደርሱ የሚችሉ ፆታዊ ጥቃቶችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል የአቋም መግለጫም አውጥቷል።

በመድረኩ ላይ የሀይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ አረጋዊያንና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

የፆታዊ ጥቃት ንቅናቄ መርሀ ግብሩ ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ”ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚከናወን ተመላክቷል፡፡

በአይናለም አባይነህ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review