ናይጄሪያ ከጋቦን ፣ ካሜሩን ከዲሞክሪቲክ ኮንጎ ፦ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ለማግኘት የሚያደርጉት ፍልሚያ

You are currently viewing ናይጄሪያ ከጋቦን ፣ ካሜሩን ከዲሞክሪቲክ ኮንጎ ፦ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ለማግኘት የሚያደርጉት ፍልሚያ

AMN – ህዳር 04/2018 ዓ/ም

የአፍሪካ ዞን የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዘጠኝ በቀጥታ ያለፉ ሀገራትን አሳውቋል።

አህጉሪቱ ተጨማሪ ሀገር እንዲወክላት የሚያስችል ጥሎ ማለፍ ላይ ለመሳተፍ አራት ሀገራትን ታፋልማለች።

በምድብ ማጣሪያው ሂደት በተሻለ ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁ አራት ቡድኖች ዛሬ ይጫወታሉ።

ምሽት 1 ሰዓት ናይጄሪያ ከጋቦን ፣ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ደግሞ ካሜሩን ከዲሞክራቲክ ኮንጎ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።

ሁለቱም ጨዋታዎች በሞሮኮ የሚደረጉ ይሆናል። አሸናፊዎቹ ሁለት ሀገራት ከሦስት ቀናት በኋላ በፍፃሜ ይጫወታሉ።

የፍፃሜው አሸናፊ ሀገር በተመሳሳይ ከሌላ አህጉር ከሚመጡ ሀገራት ጋር መጋቢት ወር ላይ የመጫወት እድል ያገኛል።

አፍሪካን የሚወክለው ሀገር አሸናፊ መሆን ከቻለ የአህጉሪቱን ኮታ ወደ 10 ከፍ ያደርጋል።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review