የሄሞራጂክ ፊቨር የተሰኘ በሽታ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ

You are currently viewing የሄሞራጂክ ፊቨር የተሰኘ በሽታ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መከሰቱን የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቁ
  • Post category:ጤና

AMN ህዳር 3/2018

የጤና ሚኒሰቴር፥ ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከከልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በአሁኑ ወቅት በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ ምንነቱ በመረጋገጥ ላይ ያለ የሄሞራጂክ ፊቨር (Hemorrhagic Fever) በሽታ መከሰቱን የቅኝት መረጃዎች ያመላከቱ መሆኑን አስታዉቋል።

በመረጃዉ መሠረት እስከአሁን ድረስ ስምንት ሰዎች (08) በበሽታው የተጠረጠሩ መሆናቸዉ ተረጋግጧል።

በዚህም መሰረት የጤና ሚኒሰቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልሉ ጤና ቢሮ ጋር በመሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ከልል የተመዘገበውን ይህንን በሽታ መንስኤውን ለማወቅ እና ተጨማሪ ስርጭቱን ለመግታት እንዲሁም ለመቆጣጠር ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደ ቦታው በመላክ የመስከ ግምገማዎች እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እያከናወነ መሆኑን በመግለጫው አመላክቷል።

በተጨማሪም የማህበረሰብ ቅኝት፣ የንከኪ ልየታ፣የቤት ለቤት ልየታ እንዲሁም የህከምና አገልግሎት አሰጣጥን እያጠናከረ ይገኛል።

ስለሆነም መላዉ ሕብረተሰባችን እና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሌላ ተጨማሪ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ፣ ለመከላከል የሚከተሉትን ምከረ-ሃሳቦች እና ጥንቃቄዎች ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

👉በአፍ፣ በአፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ክፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልከት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ እንደሚገባ፤

👉 ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ጊዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም እንደሚያስፈልግ፤

👉ሁልጊዜ እጅን በውሃና በሳሙና ወይም በሳኒታይዘር በመታጠብ ማጽዳት፣

👉ማንኛውም ጤና ተቋም በታካሚዎች ልየታ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት የቫይራል ሄሞሬጅከ ፊቨር (Viral Hemmoragic Fever) መሰል በሸታ መለየት፣ መመርመር፣ ማከም እና ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

በተጨማሪ መረጃዎችን ወደ 8335 እና 952 ነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ማግኘት እንደሚቻል ተመላክቷል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review