ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 4ኛውን ዓመታዊ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ማስጀመራቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ 4ኛውን ዓመታዊ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ ማስጀመራቸዉን ገለጹ

AMN – ህዳር 04/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ 4ኛውን ዓመታዊ የማዕድን እና ቴክኖሎጂ ኤክስፖ (MINTEX Ethiopia 2025) በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በይፋ ከፍተናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ምድሯም ልጆቿም ሀብታሞች ናቸው እስክንባል ድረስ ለአፍታም አንቆምም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ምድሯ ባለ ሦስት ድርብ ሀብት የያዘ ነው። የከርሰ ምድር ሀብቶች፣ የገጸ ምድር ሀብቶችን እና ልዩ የአየር ንብረትን ታድላለች።

ይህን ድልብ ሀብት ከነበረበት የመረሳት አባዜ በማላቀቅ ለሁለንተናዊ ብልፅግና ማሳኪያ ለመጠቀምና የኢትዮጵያን ዕድገት ለማረጋገጥ ጉዞ ጀምረናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

መንግሥት የሰጠው ልዩ ትኩረትና የወሰዳቸው እርምጃዎች ለዘርፉ መነቃቃት እና ተስፋን በማምጣት በማዕድን ኢንቨስትመንትና ወጪ ንግድ ከፍተኛ እመርታን ፈጥረዋል።

ዓለም አቀፍ ኤክስፖው ባለድርሻ አካላትን፣ ባለሀብቶችን፣ የቴክኖሎጂ አምራቾችን እና ምሁራንን በማሰባሰብ ያሉንን መልካም ዕድሎች የምናሳይበት እና ተግዳሮቶችን በቅንጅት የምንፈታበት ወሳኝ መድረክ ነው ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review