20ኛዉ የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ተፈጥሯዊ እና ሰዉ ሰራሽ ሀብቶች እንድሁም የኢትዮጵያዊያን አብሮነት ለአለም የሚታይበት መሆኑ ተገለጸ።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) ለበዓሉ እየተደረገ ያለዉን ዝግጅት በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በዓሉ የሀገር ፀጋ እና የህዝብ አብሮነትን በሚያጎላ መልኩ ይከበር ዘንድ የቅድመ ዝጎጅት ስራዎች መጠናቀቃቸዉን ገልፀዋል፡፡
በዓሉ ከህዳር 25 እስከ ህዳር 29 በተለያዩ ስያሜዎችና መርሀ ግብሮች ይከበራል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በበዓሉ ላይ የህዝብ ለህዝብ መግባባት እና ትዉዉቅን በማላቅ ለሀገር ስኬት ይመከራል ብለዋል፡፡
በዓሉ ኢትዮጵያን በሚመጥን መልኩ ይከበራል ያሉት እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) የህዳሴ ግድብን ጨምሮ እንደ ሀገር የተመዘገቡ ስኬቶች በኢትዮጵያዊያን በጋራ ይዘከራሉ ብለዋል፡፡
በቀጣይ ቀናት የክልሉን ተፈጥሯዊ እና ሰዉ ሰራሽ ሀብቶች ማስተዋወቅ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የመገናኛ ብዙሀን ጉብኝት እንደሚደረግም በመግለጫዉ ተነስቷል፡፡
በተመስገን ይመር