ከንቲባ አዳነች አቤቤ በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተቀመጡ ዋና ዋና ግቦችን ወደ እቅድ በመቀየር በዉጤታማነት መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከከተማዉ አመራሮች ጋር መምከራቸዉን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የተቀመጡ ዋና ዋና ግቦችን ወደ እቅድ በመቀየር በዉጤታማነት መተግበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከከተማዉ አመራሮች ጋር መምከራቸዉን ገለጹ

AMN ህዳር 05/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ “በመደመር መንግስት እይታ፣ የዘርፎች እምርታ” በሚል መሪ ሃሳብ ለብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በተሰጠው ስልጠና ላይ በጠቅላይ ሚኒስትራችን እና የፓርቲያችን ፕሬዚዳንት ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተቀመጡ ዋና ዋና ግቦችን ወደ እቅድ በመቀየር በከተማችን አዲስ አበባ በላቀ አፈፃፀም እና ውጤታማነት ለመተግበር ከከተማችን አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

እንደ ከተማ የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በጠንካራ የአመራር ቁርጠኝነት፣ በፈጠራ እና ፍጥነት መርህ ግቦቹን ለማሳካት የተዘጋጀውን ዝርዝር እቅድ የጋራ አድርገናል።

ከተለዩት ዋና ዋና ግቦች መካከል የብሄራዊ መታወቂያ ምዝገባን (የፋይዳ ምዝገባ)፤ የ5 ሚሊዮን ኮደሮችን፤ የተጀመሩ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳር ልማት እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን፣ ለምርጫ ምቹ ሁኔታን መፍጠር እና የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም ግቦችን መቶ በመቶ ማሳካት፤ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፤ ሌብነት፣ ጉቦኝነትንና ብልሹ አሰራርን፣ በመንደርተኝነትን፣ በአካባቢዊነት ማሰብና መስራትን እና ጠባቂነትን መቀነስ፤ እንዲሁም ተረጂነትንና ልመናን፣ ለልማት መዋል የሚገባውን መሬት አጥሮ ማስቀመጥ፣ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ እና ሰላማዊ ሁኔታን የሚያውኩ የጥፋት እንቅስቃሴዎችን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የዋና ዋና ግቦች የትኩረት ማዕከል ሆነው የሚፈፀሙ ይሆናል።

ግቦቹን ለማሳካትና ለውጤታማነታቸው እንደ ወትሮው ትዉልድና ተቋምን እየገነባን በተለወጠ የስራ ባህል 24/7 በትጋት እና በቁርጠኝነት የምንሰራ ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review