አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

AMN – ህዳር 05/2018 ዓ.ም

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ስምምነቱ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን በመጠቀም ከንግዱም ከሸማቹም ማህበረሰብ ጋር በሰፊዉ ለመድረስ አስቻይ መደላድልን ይፈጥራል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ናቸው።

ጣቢያዉ በመዲናዋ በሚገኙ አምስቱም የገበያ ማዕከላት በመዘዋወር ለማህበረሰቡ ስላለዉ የአቅርቦት እና የግብይት ስርዓት ተደራሽ ከማድረጉም ባሻገር በዘርፉ እየተሰሩ ስላሉ የቁጥጥር ስራዎችም በስፋት ሲያሳዉቅ መቆየቱን ኃላፊዋ አንስተዋል።

የዛሬዉ ስምምነትም ከጣቢያዉ ጋር በይበልጥ ተቀራርቦ ለመስራት እና የመረጃ ተደራሽነቱን ለማስፋት ጉልህ አስተዋዕፆ እንዳለዉ ገልፀዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የትዉልድ ድምፅ ከመሆኑም ባሻገር ለከተማው ነዋሪ ቀዳሚዉ የመረጃ ምንጭ እንደመሆኑ በንግድ ስርዓቱ ላይ ስላሉ አጠቃላይ እንቅስቃሴዎች ለአድማጭ ተመልካች ሲያደርስ መቆየቱን የ ኤ ኤም ኤን ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ ገልፀዋል።

የህዝቡን ፋላጎት መነሻ በማድረግም ጣቢያዉ ቀደም ሲል ከሚሰራዉ የከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ፣ የቁጥጥር ስራ እና በተለይ የገበያ ማዕከላትን የአቅርቦት የዋጋ እንዲሁም ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በስፋት ተደራሽ ለማድረግም የዛሬዉ ስምምነት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለዉን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት እያደረገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

በትባረክ ኢሣያስ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review