በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተሰሩ የልማት ስራዎች በመንግስት የሚገቡ ቃሎችን በተግባር ያረጋገጡ ናቸው

You are currently viewing በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተሰሩ የልማት ስራዎች በመንግስት የሚገቡ ቃሎችን በተግባር ያረጋገጡ ናቸው
  • Post category:ልማት

‎AMN ህዳር 5/2018 ዓ.ም

‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተሰሩ የልማት ስራዎች በመንግስት የሚገቡ ቃሎችን በተግባር ያረጋገጡ መሆናቸዉን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ ገለፁ፡፡

‎ሚኒስትር ዴኤታዉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተመልክተዋል፡፡

‎በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳዕና ከተማ ላይ የተሰራዉ የኮሪደር ልማትን የጎበኙት አቶ ተስፋሁን ፣ በአዲስ አበባ ከተማ የተሰራው የልማት ስራዎች ከተማን የመገንባት ብቃት ያረጋገጡ ስለመሆናቸው አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የኮራደር ልማት ተሞክሮ በክልል ከተሞች ላይም እዉን በማድረግ ከተሜነትን ለማስፋት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

‎ፕሮጀክቶችን መጀመር በተያዘላቸዉ ጊዜ ይጠናቀቁ ዘንድ ሁለንተናዊ ርብርብን በማድረግ ለህዝብ ግልጋሎት ክፍት ማድረግ የመንግስት መለያ መሆኑን አመላክተዋል።

‎ሚኒስትር ደኤታዉ በማዕከላዊ ኢትዮጵያም ይህ የመንግስት ልዩ መገለጫ በዉል እየታየ ነዉ ብለዋል፡፡

‎በቀጣይም ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሀገርንወደ ተሻለ እድገት የሚያስፈነጥሩ ልማቶች በመላ ሀገሪቱ ተግባራዊ እየተደረ ይገኛል ብለዋል።

‎ከዚህ በተጨማሪ መገናኛ ብዙሀን የልማት አቅሞችን እና የህዝብ አብሮነት እና ተጠቃሚነትን ማሳየት እና ማስገንዘብ ላይ ሊሰሩ እንደማገባም ሚኒስትር ዴኤታዉ አንስተዋል፡፡

‎በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review