የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሕግና ስርዓትን ተከትሎ ለመስራት የሚያስችል የመተዳደሪያ ደንብ ላይ ሰልጠና እየሰጠ ነው።
በስልጠና መድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አዲስ መሃመድ በሀገሪቱ ጠንካራ፣ ዘላቂና እውነተኛ የዲሞክራሲ እና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ለመገንባት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በመሆኑም ይህ ሚናቸው እንዲሳካ ለተለያዩ የምክር ቤቱ አደረጃጀቶች የጋራ ምክር ቤቱ የመተዳደሪያ ደንብ ላይ የአቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን አመላክተዋል።
ስልጠናው የጋራ ምክር ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት እና ሕግና ስርዓትን ተከትሎ ባለመሰራቱ ሊከሰት የሚችሉ የስነ ምግባር ጉድለቶችን ለማረም የሚረዳ መሆኑ ተነስቷል ።
የጋራ የምክር ቤቱ አባላት ከስልጠናው በኃላ አዲስ ሞሶብን እና አራዳ ፓርክን ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
በዳንኤል መላኩ