ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንጋፋው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታልን የሚመጣጠን ማስፋፊያ ተገንብቶ፤ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ተሟልቶለት ስራ መጀመሩን ገለጹ

You are currently viewing ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአንጋፋው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታልን የሚመጣጠን ማስፋፊያ ተገንብቶ፤ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ ተሟልቶለት ስራ መጀመሩን ገለጹ

AMN ህዳር 6/2018

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ዛሬ በአንጋፋው የዘዉዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል አዲስ ሆስፒታልን የሚመጣጠን ማስፋፊያ ገንብተን፤ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያ አሟልተን ስራ አስጀምረናል ብለዋል፡፡

በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የተገነባው የላቀ የሕክምና ማዕከል፣ በ1 ሺህ 800 ካ.ሜ ስፋት ላይ ያረፈ እና ባለ 10 ወለል ህንፃ ሲሆን ለተኝቶ ታካሚዎች አገልግሎት የሚሰጥ 320 አልጋ አለው። ይህም ላለፉት 91 ዓመታት የነበረውን የዘውዲቱ ሆስፒታል ታካሚ አገልግሎትን በእጥፍ ያሳድገዋል ብለዋል፡፡

ሆስፒታሉ ለህክምና ባለሙያው እና ለታካሚው በሚመች መልኩ የተገነባ ሲሆን አሁን ላይ የህክምናው ዘርፍ በደረሰበት ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎች የተደራጀ እና የራሱ ኦክስጂን ማምረቻ ጭምር ያለው ነው።

ይህ ሆስፒታል አስተዳደራችን አዲስ አበባን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለጀመረው ሥራ ተደማሪ አቅም የሚፈጥር ይሆናል ሲሉ ገልጸዋል፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review