ባለፉት አመታት በቱሪዝም ዘርፋ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገርን ገፅታ ለሀገር ዉስጥ እና ለአለም አቀፍ ጎብኝዎች ማሳየት ተችሏል

You are currently viewing ባለፉት አመታት በቱሪዝም ዘርፋ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገርን ገፅታ ለሀገር ዉስጥ እና ለአለም አቀፍ ጎብኝዎች ማሳየት ተችሏል

AMN ህዳር 6/2018

የኢፌድሪ መንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ የሀምበርቾ ተራራን በጎብኙበት ወቅት እናዳሉት ባለፉት አመታት በቱሪዝም ዘርፋ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገርን ገፅታ ለሀገር ዉስጥ እና ለአለም አቀፍ ጎብኝዎች ማሳየት ተችሏል፡፡

በ777 ደረጃዎቹ የሚታወቀዉ የሀምበርቾ ተራራ ለሀገር ዉስጥ እና ዐለም አቀፍ ጎብኝዎች የስበት ማዕከል ይሆን ዘንድ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሰጡት ትኩረት ዳግም 777 ደረጃዎች ተገንብተዉለታል፡፡

ባለፉት የለዉጥ አመታት ለቱሪዝም ዘርፉ የተሰጠ ትኩረት ለበርካታ መዳረሻዎች መልማት እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ ለመሆን መነሻ ሆኗል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዉ ይህ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

በቱሪ ዝም ዘርፉ አንድም የሀገርን ገፅታ ማሳየት በሌላ መልኩ ደግሞ የስራ እድል መፍጠር ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዉ ሀምበርቾ ለዚህ ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው የሀገርን የቱሪዝም ፀጋ ለአለም ማሳየት ላይ በቀጣይም ይሰራል ብለዋል፡፡

በተመስገን ይመር

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review