በቀጣዮቹ 8 ወራት በመዲናዋ የኑሮ ውድነት ጫናን የሚቀነሱ የምርት አቅርቦት ፣ ግዥና ቁጥጥር ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናገሩ ::
በፌዴራል መንግስት ከተቀመጡ የእቅድ አይነቶች መከከል የመቀነስ እቅድ አንዱ ሲሆን ለዚሁ መነሻነት በአዲስ አበባ ከተማ የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ ወደስራ ገብቷል::
ግብረ ሃይሉ በሚቀጥሉት 8 ወራት በሚያከናውናቸው የኑሮ ውድነት ቅነሳ እቅዶች ላይ ምክክር እያካሄደ ነዉ።
እቅዱን ለመተግበር ማምረት፤ መግዛትና መቆጣጠር የሚሉ የመፍትሄ ሃሳቦች ዋና ጉዳዮች መሆናቸውም ያነሱት የአዲስ አበባ ም/ ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊው አቶ ጃንጥራር አባይ የምርት አቅርቦትን መጨመር ፣ የቅዳሜና እሁድ ገበያ መደረሻ ቦታዎች ቊጥርን ከ219 ወደ 240 ማሳደግና ምርቶችን መጨመር ፣ ሽማች ማህበራትን ማሳደግ ፣ የዳቦ ፋብሪካዎች መደገፍና ቁጥር መጨመር ፣ የተኪና ኤክስፖርት ምርቶችንና ጥራት ማሳደግ ትኩረት የሚደረግባቸው መሆናቸውን ገልፀዋል ::
ለዚህ ስኬት የግብረ ሃይሉ አባላትና ተቋማት ተናበዉና ተቀናጅተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል ::
በአንዋር አህመድ
ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ምርጫዎ ያድርጉ ! የትዉልድ ድምጽ ! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork