መንግሥት በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎች እንዲታወቁ ፣እንዲለዩ እና እንዲገለጡ የሰጠው ትኩረት የብልፅግና አቅሞች እንዲደመሩ አስችሏል

You are currently viewing መንግሥት በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎች እንዲታወቁ ፣እንዲለዩ እና እንዲገለጡ የሰጠው ትኩረት የብልፅግና አቅሞች እንዲደመሩ አስችሏል

AMN- ህዳር 7/2018 ዓ.ም

እንደ አገር በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎች ታውቀውና ተለይተው የህዝቡ የኢኮኖሚ መሠረቶች እንዲሆኑ ለማስቻል እየተደረጉ ያሉ ጥረቶች ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ተደማሪ አቅምን መፍጠር ችለዋል ።

መንግሥት በኢትዮጵያ ያለወን የቱሪዝም አቅም በመገንዘብ ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ክልሎች በአካባቢው የሚገኙ ፀጋዎች አልምተው ዜጎቻቸውን ተጠቃሚ እንዲያደርጉ መልካም ዕድል እየፈጠረ ይገኛል ።

በተለይ የቱሪዝም መዳረሻ ቦታዎች እንዲጠበቁ እና አንዲለሙ በማድረግ የጎብኝዎችን ቁጥር ለማሳደግ እና የጎብኚዎችኝ የቆይታ ጊዜ በማራዘም ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ከፍ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት እንደ ሀገር ዕመርታ የታየበት ነው፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምስራቅ ጉራጌ ዞን ከሚገኙ የቱሪዝም መዳራሻዎች መካከል ዓለም አቀፍ የጥያ ትክል ድንጋይ ቅርሶች እና ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ-መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም የሚጠቀሱ ናቸው።

ጥያ ትክል ድንጋይ ዓለም አቀፍ መካነ ቅርስ ተብሎ በ1972 ዓ.ም በዩኒስኮ የተመዘገበ ቢሆንም ለዘመናት ትኩረት ተነፍጎት የቱሪዝም መሠረተ ልማቶች ሳይሟሉለት ቆይቷል ።

የኢትዮጵያ ጸጋዎችን ሁሉ አሟጦ መጠቀም በሚል በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት መካነ ቅርሱ የኢትዮጵያ ተደማሪ አቅም እንዲሆን በሚያስችል መልኩ የተለያዩ መሠረተ ልማቶች እየተሟሉለት ይገኛል ።

በአካባቢው ያለው የቱሪስት እና የተመራማሪዎች ፍሰትን በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ያደርጋል በሚል የሚጠበቀው “ጥያ ፕሮጀክት” ሁለት ከተሞችን የሚያገናኝ፣ ባለሀብትን በማስተባበር የሚሰራ እና ከ3.5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈልግ ነው።

የጢያ ትክል ድንጋይ ፕሮጀክት ለበርካታ ዜጎች ቆሚና ጊዜያዊ የሥራ ዕድል መፈጥር የቻለ ሲሆን እንደ አገር የአከባቢው ፀጋ የሚገለጥበት ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ሲል የኢፌድሪ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መረጃ ገልጿል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክን ምርጫዎ ያድርጉ ! የትዉልድ ድምጽ ! https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#addismedianetwork

#Ethiopia

#addisababa

#postviralシ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review