የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመመርመር የሚያስችል ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ ወደ ስፍራው እየተላከ ነው

You are currently viewing የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመመርመር የሚያስችል ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ ወደ ስፍራው እየተላከ ነው

AMN – ህዳር 8/2018 ዓ.ም

የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመመርመር የሚያስችል ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪ ህመሙ ወደ ተከሰተበት ደቡብ ኢትዮጵያ ጂንካ እየተላከ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ጤና ሚኒስቴር በደቡብ ኢትዮጵያ የተከሰተውን ማርበርግ ቫይረስ በሽታ አስመልክቶ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።

በማርበርግ ቫይረስ በሽታ እንደተከሰት ከታወቀበት ህዳር 3 ቀን ጀምሮ 17 ናሙናወች በበሽታው ከተጠረጠሩ ግለሰቦች የተወሰደ ሲሆን፣ ሶስት ሰወች በበሽታው እንደተያዙም ተረጋግጧል።

ስድስት ያህል ምልክት የታየባቸው ሰወች ግን ምርመራ ተደርጎላቸው ሳይረጋገጥ ህይወታቸው ማለፉን የጤና ሚንስቴር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ተናግረዋል።

በሽታው በ1967 ዓ.ም. የጀርመኗ ከተማ ማርበርግ ከተማ እንደተከሰተ በመግለጫው የተጠቃመ ሰሆን እስካሁን የታወቀ መድሀኒት ይፍ ባለመሆኑ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የህመሙ ምልክቶች

➪ ከፍተኛ የሆነ ትኩሳት

➪ ከአፍ ፣ ከአይን ፣ ከአፍንጫ እና ከተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች ደም መፍሰስ

➪ ራስ-ምታት

➪ ማቅለሽለሽ እና ማስመለስ

➪ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም

➪ ድካም እና የሰዉነት መዛል

➪ የቆዳ ላይ ሽፍታና መበለዝ

ለሄሞራጂክ ፊቨር በይበልጥ ተጋላጭ የሆኑት እነማን ናቸው?

የህመሙ ምልክት ወዳለበት ቦታ የጉዞ ታሪክ ያላቸዉ

የህመሙ ምልክት ከታየባቸዉ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸዉ

ስለመሆነም ተጠቀሟል።

ህመሙን በቀጥታ ማከም የሚያስችል መድሀኒት ባይኖርም ምልክቶቹን እና ሌሎች ጉዳቶችን መቀነስ የሚያስችል የህክምና እርዳታ ይሰጣልም ብለዋል፡፡

ምርመራውን ለማድረግ እንደቻል ወደ ጅንካ ተንቀሳቃሽ ላብራቶሪን መላክ ጨምሮ በርካታ የህክምና ባለሙያወች በየክልሉ ዝግጅት እንዲያደርጉ ስራወች በስፍት እየተሰሩ ስለመሆኑ ተጠቁሟል።

ለተጨማሪ መረጃዎች ፦ ወደ 8335 እና 952 በነፃ መደወል እንደመቻልም በመግለጫው ተመላክቷል።

ቤተልሔም አየነው

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review