ጀርመን ስሎቫኪያን 6ለ0 በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ አለፈች

You are currently viewing ጀርመን ስሎቫኪያን 6ለ0 በማሸነፍ ለዓለም ዋንጫ አለፈች

AMN-ህዳር 9/2018 ዓ.ም

ጀርመን ስሎቫኪያን በማሸነፍ የ2026 የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋን አረጋግጣለች።

በሬድ ቡል አሬና በተደረገው ጨዋታ ጀርመን 6ለ0 ማሸነፍ ችላለች። ሊሮይ ሳኔ (ሁለት) ፣ ኒክ ቮልትማደ ፣ ሰርጅ ግናብሪ ፣ ሪድል ባኩ እና አሳኔ ኦድራጎ የጀርመንን ስድስት ግቦች አስገኝተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ጀርመን ምድብ አንድን በበላይነት አጠናቃ የዓለም ዋንጫ ተሳታፊ ሆናለች። ስሎቫኪያ በጥሎ ማለፍ ዙር ትሳተፋለች።

በምድብ ሊቱኤኒያን የገጠመችው ኔዘርላንድስ 4ለ0 በማሸነፍ የዓለም ዋንጫ ትኬቷን አግኝታለች። ቲጃኒ ራይንደርስ ፣ ኮዲ ጋክፖ ፣ ዣቪ ሲሞንስ እና ዶኒየል ማለን አራቱን ግቦች ከመረብ አሳርፈዋል።

በዚሁ ምድብ ፖላንድ ማልታን 3ለ2 በማሸነፍ 2ኛ ሆና አጠናቃለች። በሮበርት ሌቫንዶቭስኪ አምበልነት የምትመራው ፖላንድ ሌላኛዋ የጥሎ ማለፍ ዙር ተሳታፊ ሀገር ሆናለች።

በሸዋንግዛው ግርማ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review