ሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በሆስፒታሎች ስብራትን እና የአጥንት መሰንጠቅን ለመለየት እና ፈጣን ህክምና በመስጠት ረገድ ዶክተሮችን እንዲያግዝ ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል።
በሰሜን ሊንከንሻየር እና በጉል ኤን ኤች ኤስ ፋውንዴሽን ትረስት የሚገኘው የአደጋ ጊዜ መምሪያዎች፣ ከዚህ ወር በኋላ በሚጀመረው የሁለት ዓመት የኤን ኤች ኤስ ኢንግላንድ የሙከራ እቅድ ውስጥ ይሳተፋሉ ተብሏል።
የአደጋ ጊዜ ህክምና አማካሪ የሆኑት አብዱል ካን፣ ችግሮችን ለመለየት የኤአይ ቴክኖሎጂን መጠቀም በሰሜን አውሮፓ ያለውን ፍላጎት ለማሟላት እንደሚያግዝ መታየቱን በመግለፅ፣ በሌላም ቦታ ተመሳሳይ ፍላጎት እንዳለ ለመለየት ደስተኞች መሆናቸውን ተናግረዋል።
የኤአይ ሶፍትዌር ክሊኒኮችን በምርመራ ወቅት እገዛ ለማድረግ እንደ ተጨማሪ መሳሪያ ጥቅም ላይ እንደሚውል ፋወንዴሽኑ አመላክቷል።
ቴክኖሎጂው ከሁለት ዓመት በታች ባሉ ህፃናት እና የደረት፣ አከርካሪ፣ የራስቅል፣ ፊት ላይ ወይም በሌሎች ለስላሳ ህበረ ህዋሳት ባሉባቸው ክፍሎች ጥቅም ላይ እንደማይውል ፋወንዴሽኑ አያይዞ ገልጿል፡፡
በታምራት ቢሻው