በአብሮነት፣ውበት፣ ፍቅር እና ህብረትን ያደመቁ ብሩሾች

You are currently viewing በአብሮነት፣ውበት፣ ፍቅር እና ህብረትን ያደመቁ ብሩሾች

AMN- ሕዳር 09/2018 ዓ.ም

‎ውበት፣ ፍቅር ፣አብሮነት ፣ ስሜት፣ ቀለም፣ ሀሳብ፣ ጀግንነት ፣ህብረት፣ተፈጥሮ እና ሌሎችንም የእለት ተዕለት ሂደቶች በስዕል ይገለፃሉ።

‎እነዚህን እና ሌሎችን የሰው ልጅ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ሰዓሊያን በስዕሎቻቸው የሚሰማቸውን ውይም የገባቸውን ለማጋባት ይጥራሉ።

‎እነዚህ ሂደቶች የተገለጡበት የስዕል አውደ ርእይ በአዲስ አበባ ከህዳር 3 እስከ 29 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆይ ለህዝብ ክፍት በተደረገው “አብሮነት” በተሰኘው የቡድን የስዕል አውደ ርዕይ ለጥበብ ወዳጆች ተደግሷል።

‎አውደ ርዕዩ በሰዓሊ ብሩ ወርቁ፣ ሰዓሊ ያሬድ ወንድሰን እና ሰዓሊ ዘውዱ ገብረሚካኤል የተሳሉ የተለያዩ ሀሳቦችን ያዘሉ የስዕል ስራዎቻቸውን በአብሮነት በፈንድቃ የባህል ማዕከል ለዕይታ ቀርበዋል።

‎ሰዓሊ ዘውዱ ገብረሚካኤል ፣ 12 ስራዎችን በስዕል አውደ ርእዩ ይዞ መቅረቡንና የስራዎቹ ዋና ጭብጥ አፍሪካን የሚያንፀባርቁ መሆናቸውን ነው የገለፀልን ።

‎የስዕሉ መነሻ ሀሳብ ኢትዮጵያ ቀለም ያለው በአገር በቀል ፊደላት የተሽሞነሞኑ ፣በቀለማት የተዋቡ የስዕል ስራዎች መሆናቸውን ነው ሰዓሊ ዘውዱ ያጫወተን ።

አብሮነት የሚለውን ርዕስ የስዕል አውደ ርእዩ መጠሪያ ሲሆን መነሻውም የስዕል ስራዎች ውስጥ የአፍሪካ ህብረትን የሚንፀባርቅ በአፍሪካ ያሉ ጥበቦችን በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ የማስቀመጥ ሀሳቦችን ያዘሉ በመሆናቸው ነው ሲል አርቲስት ዘውዱ ተናግሯል።

‎በመዲናዋ ከዚህ ቀደም የነበሩ የስነ-ጥበብ ስራዎች የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እንደነበረው በማስታወስ ጋለሪዎች በበዙ ቁጥር ህብረተሰቡ ከጥበብ ጋር የሚገናኝበት አጋጣሚ ሰፊ እንዲሆን ማስቻሉን ነው ምልከታውን ያጋራን።

‎ሰዓሊ ብሩ ወርቁ በበኩሉ በአውደ ርእዩ ይዞ የቀረባቸው ስእሎች ፍቅር እና ውበትን የሚያሳዩ ወይም የሚጠቁም መልዕክት ያላቸውን መሆናቸውን ይናገራል።

‎በፍቅር እና በውበት ውስጥ በግዜ እና ወቅት መሀል ያለውን ሂደት የሚያሳይ ሲሆን ቀለማቶቹም ስሜትን የሚነኩ ሞቅ የሚያደርጉ የሚያስደስቱ መሆናቸውን ነው የተናገረው ።

‎ከተፈጥሮ ጋር የተጣመሩ 12 የስዕል ስራዎችን ማቅረቡንና ፣ ስዕሎቹ አበቦች ሲሆኑ ከሰው ልጅ ጋር የደስታ እና የሀዘን ስሜት የሚገለፅባቸው እንዲሁም አበባ እና የሰውን ልጅ ቁርኝነት የተገለፀባቸው መሆኑን ነው የተናገረው ።

‎አበቦች ላይ ያሉ ስሜቶኝን ከሴቶች ተፈጥሮ ጋር በማዛመድ የሁለቱንም ውበት ፣ የተፈጥሮ ስጦታዎች በስዕሉ ለመግለፅ መሞከሩን ነው የገለፀው።

‎ሰዓሊ ያሬድ ወንድወሰን በአብሮነት የስዕል አውደ ርዕይ ስራዎቹን ካቀረቡ ሰአሊዎች አንዱ ነው ፡፡ ስዕሎቹ በአከባቢው የሚሰማውን አልያም የሚያየውን ስሜቶች በሙሉ የገለፀበት መሆኑን ይናገራል ።

‎በከተማ ፣በገበያ ፣በሀይማኖት ተቋማት እና በተለያዩ ቦታዎቸ የተሰማውን ስሜት በስዕሉ ማሳየት መቻሉን ነው የገለፀው።

የሰው ልጆች በመሰጠት፣ በመውደድና እና በፍቅር በሚያከናውኗቸው የእለት ተእለት ስራዎች ላይ የስዕል ጥበብ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል ስለሆነም የስዕል ጥበብን የዜጎችን አስተሳሰብ ለመግራት እና ለመቀየር እንዲሁም ለማስተማር ድርሻው የጎላ መሆኑን ሰአሊዎቹ አንስተዋል።

‎በሔለን ተስፋ

#አዲስሚዲያኔትዎርክ

#addismedianetwork

#Ethiopia

#addisababa

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review