መንግሥት ለኢንቨስትመንት የሰጠው ትኩረት በጉራጌ ዞን ተጨባጭ ውጤትን አስገኝቷል

You are currently viewing መንግሥት ለኢንቨስትመንት የሰጠው ትኩረት በጉራጌ ዞን ተጨባጭ ውጤትን አስገኝቷል

AMN ህዳር 9/ 2018 ዓ.ም

የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለማጠናከር መንግሥት እያደረገ ያለው ጥረት በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የጉራጌ ዞን ተጨባጭ ውጤትን እያስመዘገበ መሆኑን የዞኑ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገልጿል፡፡

በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች እና እየተመዘገቡ ያሉ ውጤቶች እንደ ሀገር መንግሥት ለዘርፉ የተሰጠውን ትኩረት የሚያመላክት ነው፡፡

የአገር ውስጥ ባለሀብቶች በኢንቨስትመንትና በግብርና ልማት እንዲሰማሩ ለማበረታታት መንግሥት በወሰደው ቁርጠኝነት እና በፈጠረው አስቻይ ሁኔታ በርካታ ዜጎች በተለያዩ የምርት ሥራዎች ላይ ተሰማርተው አገራዊ ዐቅምን የሚያጎለብት ትርጉም ያለው ውጤት እያስመዘገቡ ይገኛል፡፡

በዞኑ የተጀመረው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ለብዙ ዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ፣ በአገር አቀፍ ደረጃ የገበያ ሁኔታን በማረጋጋት ረገድ ተጨባጭ እና ተስፋ ሰጪ ውጤቶች የታዩበት ነው፡፡

መንግስት ኤክስፖርትን ለማበረታታት በተከተላቸው የፖሊሲ ማሻሻያዎችን በወሰዳቸው ወሳኝ ርምጃዎች ክልሉ እንደ አትክልትና ፍራፍሬ፣ ቅመማ ቅመሞች፣ የቅባት እህሎች፣ እና አቮካዶ የመሳሰሉትን ምርቶች ወደ ውጭ ገበያ በመላክ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ማምጣት ተችሏል፡፡

በዞኑ 155 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች በግብርናው የተሰማሩ ሲሆን፣ ከ11 ሺህ 200 ሄክታር በላይ የሚሆን መሬትም በግል ባለሀብቶች እንዲለማ ተደርጓል፡፡ በ2017 የምርት ዘመን ከጉራጌ ዞን ወደ ውጭ ገበያ ከተላኩ የግብርና ኢንቨስትመንት ምርቶች 8.9 ሚሊዮን ዩሮ የውጭ ምንዛሪ ለሀገር ማስገባት ተችሏል።

መንግሥት ለኢንቨስትመንት ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት ተከትሎ፣ በዚህ ዓመት እስከ መጀመሪያው ሩብ ዓመት ድረስ ብቻ ወደ ውጭ ገበያ ከተላኩ ምርቶች 2.8 ሚሊዮን ዩሮ ገቢ መገኘቱን ከመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ያገኘነዉ መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review