የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ማጣርያ ውድድር ሁለተኛ ጨዋታውን ከደቡብ ሱዳን ጋር አድርጎ 4:1 አሸንፏል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በመጀመሪያው አጋማሽ 2ለ0 እየመራ ቆይቶ ከእረፍት መልስ ተጨማሪ 2 ግቦችን አስቆጥሮ 4ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
በመጀመሪያው አጋማሽ ዳዊት ካሳው ለኢትዮጵያ 2 ግቦችን (13′ እና 17ኛ ደቂቃዎች ላይ) ያስመዘገበ ሲሆን ከዕረፍት መልስ 52 ኛው ደቂቃ ላይ የተገኘውን ፍፁም ቅጣት ምት ወደ ጎል በመቀየር ለራሱ ሀትሪክ የሰራበት ጎል አስቆጥሯል። በተጨማሪም እንየው ስለሺ 56ኛው ደቂቃ ላይ አራተኛ ጎል ማስቆጠር ችሏል።
በደቡብ ሱዲን በኩል 78 ኛው ደቂቃ ላይ የተገኘን ፍፁም ቅጣት ምት ፓኖም ጆው ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
በዚህም ኢትዮጵያ ደቡብ ስዳንን 4ለ1ማሸነፍ ችላለች።