በኢትዮጵያ እና በማሌዢያ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር ለማላቅ የሚያግዝ የንግድ ፎረም እተካሔደ ነው

You are currently viewing በኢትዮጵያ እና በማሌዢያ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር ለማላቅ የሚያግዝ የንግድ ፎረም እተካሔደ ነው

AMN ህዳር 10/2018

የኢትዮ – ማሌዢያ የንግድ ፎረም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከል እየተካሔደ ይገኛል።

የንግድ ፎረሙ በሁለቱ ሐገራት መካከል ያለውን የንግድ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ያሉ እድሎችን በመለየት የሁለቱ ሐገራትን የኢኮኖሚ ትስስር ለማላቅ የሚያግዝ መሆኑ ተመላክቷል።

ፎረሙ ከኢኮኖሚ ባሻገር በተለያዩ ዘርፎች የሁሉቱ ሐገራት የጋራ ብልጽግና እድሎችን ለመለየትና የሐገራቱን ግንኙነት ለማጎልበት ያስችላል ተብሏል።

በመድረኩ በኢትዮጵያና በማሌዢያ በኢንቨስትመንትና በንግድ ዘርፍ ያሉ እድሎች ላይ ገለጻ ተደርጓል።

የሁሉቱ ክፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችና የባለሐብቶች እንዲሁም የዘርፉ ተዋናይ እየተሳተፉ ይገኛል።

በሄኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review