ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በማፋጠን ከተሞቻችን ከፍተኛ ሚና አላቸው ሲሉ ገለጹ

You are currently viewing ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በማፋጠን ከተሞቻችን ከፍተኛ ሚና አላቸው ሲሉ ገለጹ

AMN ህዳር 10/2018 ዓ.ም

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸዉ ባሰፈሩት መልእክት ኢትዮጵያ ወደ ብልጽግና የምታደርገውን ጉዞ በማፋጠን ከተሞቻችን ከፍተኛ ሚና አላቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በአፋር ክልል ሰመራ – ሎጊያ ሲካሄድ የቆየውና ዛሬ በድምቀት ያጠናቀቅነው 10ኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ፎረም የከተሞቻችንን የዕደገት ጉዞና ተስፋ በግልፅ ያሳየ ነው።

የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያ የሥልጣኔ መሠረት የሆኑትን ከተሞቻችንን የብልጽግና ማሳያዎችና ማዕከላት አድርጎ ይመለከታቸዋል።

በብልጽግና ማዕከልነታቸው የብዝኃ ዘርፍ ኢንዱስትሪ ማበቢያ ቦታዎች ሲሆኑ፣ በብልጽግና ማሳያነታቸው ደግሞ የሁለይተናዊ የዕድገት ጉዟችንና የክትመት ማዘመን ሥራችን ወደ ገጠር እንዲሰፋ መሠረት እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል፡፡

በመዲናችን አዲስ አበባ የጀመርነው ከተሞችን ለብልጽግና ጉዞ የማመቻቸት እንቅስቃሴ ዛሬ ወደ አነስተኛ የገጠር ከተሞች እየደረሰ ነው፡፡ የገጠር ኮሪደር ዋና ዓላማውም ገጠሩን በአስተዳደር፣ በመሠረተ ልማትና በክትመት ሥርዓት በማስተሣሠር ወደ ከተማነት ማሳደግ ነው፡፡

በቀጣይ በከተሞቻችን የመኖሪያ ቤት እጥረትን በተለያዩ አማራጮች ማቃለል፣ ጽዳትና አረንጓዴ ልማትን የሕዝብ ባህል ማድረግ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብቶቻችንን ወደ ቱሪዝም ሀብትነት መቀየር፤ ወጣቶችን በእውቀትና ክህሎት ለሥራ ማብቃት ላይ ትኩረት ልንሰጥ ይገባል።

ለፎረሙ ስኬታማነት የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ ሁሉ እና በተለይም የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርን የአፋር ክልልና የሰመራ-ሎጊያ ሕዝብና አስተዳደርን በድጋሜ ማመስገን እፈልጋለሁ ብለዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review