ዶክተር ጂኔኑስ ፍቃዱ ተማራማሪ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በቻይና ሆንግ ኮንግ ዩኒቨርስቲ ውስጥ የድህረ ምረቃ ዶክትሬት (Post Doctoral) ትምህርቱን በመከታተል ትምህርቱን አገባዷል።
ይህ ተመራማሪ ላለፉት ሶስት ተከታታይ አመታት አመርቂ የሚባል ውጤት አስመዝግቧል፡፡
ሳንፎርድ ዩኒቨርስቲ ይህንን ተመራማሪ አስመልክቶ ሰሞኑን ያወጣው መረጃ ደግሞ የዓለም መነጋገሪ ሆኗል፡፡
ይህም ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ የምርምር ጽሁፋቸዉ በበርካቶች ዘንድ ለማጣቃሻነት ከሚውሉ የአለማችን ሁለት ፐርሰንት ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሊሆን መቻሉ ነው፡፡
የወለጋ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበረዉ ዶ/ር ጂኔኑስ በወጣትነት እድሜው በፋርማሲ ሳይንስ ይታወቃል፡፡
ከ100 በላይ የምርምር ጽሁፎችንና መጽሄቶችን በማሳተምም አለም አቀፍ እዉቅና አግኝቷል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሳንፎርድ ዩኒቨርስቲ ትምህርታቸዉን በመከታተል ላይ የሚገኙ ተማሪዎችና የተለያዩ ምርምሮችን የሚያካሄዱ ተመራማሪዎች የአለም ሳይንቲስቶች ካሳተሟቸዉ በርካታ የምርምር ጽሁፎች መካከል የዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ የምርምር ጽሁፎች የመጀመሪያዉ መሆኑን ይፋ አድርጓል፡፡
ይህንን ተከትሎም ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ በአለም ላይ ከሚታወቁ ሁለት እጅ ምሁራን አንዱ ሊሆን በቅቷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም በሆንግ ኮንግ ዩኒቨርስቲ አመርቂ ስኬት ካስዘገቡ 6 ተመራማሪዎች መካከል አንዱ ሊሆን ችሏል፡፡
”ይህ ስኬት ከፈጣሪ የተገኘ ነው፤ ለሶስት አመታት ከነዚህ ተመራማሪዎች አንዱ በመሆኑ ደስታ ይሰማኛል” ሲል ይህ ወጣት ምሁር ሃሳቡን አጋርቷል፡፡
በ2023 በ5ሺህ 445 ምርምሮች ላይ የጂኔኑስ የምርምር ጽሁፎች የተጠቀሱ ሲሆን በ2024 በ3ሺህ 148 ምርምሮች ላይ እንዲሁም በ2025 በ1ሺህ 717 ጽሁፎች ላይ ስራዎቹ በዋቢነት ተጠቅሰዋል፡፡
ዶ/ር ጂኔኑስ ፍቃዱ በወለጋ ዩኒቨርስቲ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ሲሆን እዚያዉ በመምህርነት ሲያገለግል ቆይቷል፡፡
ኋላ ላይ ግን ለተጨማሪ ትምህርት ወደ ውጪ ሃገር ተልኮ እዚህ ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል፡፡
በመልካሙ አበበ